ወደ ይዘት ዝለል
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት       Ethiopian Media Council
ቅሬታ
● ቀጥታ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የግልግል ዳኝነት አካል የውሳኔ ቁጥር 009/2018 ዜና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በትሪታ ኤፍ ኤም ጣቢያ ላይ በቀረበ የቀጥታ ስርጭት የሥነ-ምግባር ጥሰት ቅሬታን መርምሮ ውሳኔ አሳለፈ። የሀዘን መግለጫ የሙያ ብቃት መታወቂያ ጉዳይ፣ መጋቢት 09 ,2017 What’s New Mar 18, 2025 የኢትዮጵያ ሚዲያ ምክር ቤት በኢኮኖሚ ችግሮች ውስጥ ለሚሳተፉ የሚዲያ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚዲያ ፈንድ ለማቋቋም ውይይት ጀምሯል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ የሚዲያና የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ጋር በጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር ደንብ ዙሪያ በአሶሳ ከተማ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አሳሳቢነቱ በጎላው የጋዜጠኞች እሥር እና ሌሎች ጉዳዮች ከጋዜጠኞች ጋር እንዲወያዩ ጥያቄ ቀረበ
በ 6672 ይደውሉ

ስለ ኢመብም ይወቁ

ስለ እኛ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሀገሪቱ ውስጥ በመገናኛ ብዙሃን የእርበእርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግና የጋዜጠኞች የስነ ምግባር ደንብን በማስጠበቅ በኩል በኢትዮጵያ ሚዲያ ፖሊሲና እና በመገናኛ ብዙሃን ዐዋጅ ቁጥር1238/13 እውቅና ያለው ተቋም ነው።

2012/2019
113
§ I

እኛ ማን ነን

የኢትዮጵያ ፕሬስ የጋራ መድረክ

ለታማኝ ጋዜጠኝነት የእርስ በእርስ የቁጥጥር ስርዓት የሚተገብር ተቋም።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት (ኢመብም) በኢትዮጵያ ውስጥ ስነ-ምግባር፣ ሙያዊ እና ኃላፊነት የሚሰማው የሚዲያ አሰራርን ለማስተዋወቅ የተቋቋመ ነፃ እና ራስን በራስ የሚያስተዳድር ተቋም ነው። ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሚዲያ ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች፣ አሳታሚዎች፣ ብሮድካስተሮች፣ የማህበረሰብ ሚዲያ፣ የበይነመረብ ሚዲያ እና የሙያ ማህበራት ይወክላል።

ኢመብም ተጠያቂነትን፣ ሙያዊ ብቃትን እና የስነ-ምግባር ደረጃዎችን መከበር እያረጋገጠ የሚዲያ ነጻነትን ለማጠናከር ይሰራል፡፡ ምክር ቤቱ መተማመንን በማሳደግ፣ ውይይትን በማበረታታት እና ከሚዲያ ይዘት ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ከፍርድ ቤት ውጪ ባሉ እና ግልጽ በሆኑ አሰራሮች በመፍታት በሚዲያ እና በህዝብ መካከል እንደ ድልድይ ያገለግላል።

እንደ ራስን በራስ ማስተዳደሪያ የሚዲያ መድረክ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት ጋር በተጣጣመ መልኩ የመናገር ነፃነትን ይደግፋል፣ እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች በኃላፊነት እና ለህዝብ ጥቅም እንዲሰሩ ያበረታታል።

ነፃ ፕሬስ መንግሥት የሚሰጠው መብት አይደለም — ለሕዝብ የሚገባ ግዴታ ነው።
§ II

ተልዕኮ እና ተግባራት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት የሚከተሉትን ቁልፍ ኃላፊነቶች ተሰጥቶታል

  1. ሥነ-ምግባራዊ ጋዜጠኝነት

    ሥነ-ምግባራዊ ጋዜጠኝነትንና ሙያዊ መመዘኛዎችን ያበረታታል።

  2. የእርስ በእርስ ቁጥጥር

    የእርስ በእርስ ቁጥጥርንና ተጠያቂነትን ያበረታታል።

  3. የቅሬታ መፍትሄ

    ቅሬታዎችን ይቀበላል፣ ይገመግማል፣ ይፈታል።

  4. የመናገር ነፃነት

    ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ እና መረጃ የማገኘት መብትን ያስጠብቃል።

  5. አቅም ግንባታ

    ለጋዜጠኞችና ለሚዲያ ተቋማት የአቅም ግንባታ።

  6. ከባለድርሻ አካላት ውይይት

    በሚዲያ ባለድርሻ አካላት፣ በሲቪክ ማህበረሰብ እና በሕዝብ መካከል ውይይትን ያመቻቻል።

  7. የፖሊሲ አስተዋጽኦ

    በሚዲያ ፖሊሲ ህግና ደንብ ውይይትና ማሻሻያ ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ።

  8. ትብብር

    ከመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ እና ሌሎች ባለስርሻ አካላት ጋር በዓዋጅ ቁጥር 1238/13 መሰረት በትብብር መስራት።

§ III

አቅጣጫችን

ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

ራዕይ

ነፃ፣ ሙያዊ፣ ስነ-ምግባር ያለው እና የታመነ የሚዲያ ዘርፍ።

ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ ለማህበራዊ ትስስር እና ህዝባዊ ውይይትን የሚያጎለብት የመገናኛ ብዙኃንን ነጻነት ማሳደግ።

ተልዕኮ

የሚዲያን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስራዓትን ማጠናከር።

የሚዲያ ነጻነትን ማስጠበቅ ሙያዊ ብቃአትን ማጎልበት እና የሚዲያ አለመግባባቶችን መፍታት።

ዕሴቶቻችን

ስራችንን የሚመሩ መርሆዎች።

በሚዲያ ቁጥጥር ውስጥ ለላቀ ውጤት ያለንን ቁርጠኝነት የሚገልጹ መርሆች እንክተላለን።

  • ነፃነት

    ከፖለቲካዊ፣ ንግድ ወይም ውጫዊ ተጽዕኖ ነፃ

  • ታማኝነት

    ለስነ-ምግባር እና ሙያዊነት ታማኝነት

  • ግልጽነት

    ግልጽ እና ተጠያቂነት ያላቸው ሂደቶች

  • አካታችነት

    የተለያዩ የሚዲያ እና ማህበረሰቦችን ውክልና

  • የሕዝብ ጥቅም

    በኃላፊነት በተሞላ ጋዜጠኝነት ማህበረሰቡን ማገልገል

§ IV

የተቋሙ አደረጃጀት

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ድርጅታዊ መዋቅር ሥዕላዊ መግለጫ
  • ጠቅላላ ጉባኤ
    • ኦዲተር
    • ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
      • ዋና ስራ አስኪያጅ
        • ሒሳብ ሹም / ገንዘብ ያዥ
        • ጠቅላላ አገልግሎትና አስተዳደር
        • የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን
    • የዳኝነት/ግልግል አካል
      • ይግባኝ ሰሚ ፓነል
      • ዕንባ ጠባቂ
  • ከፍተኛ አካል
  • አስፈጻሚ እና ቁጥጥር
  • አስተዳደር እና ፓነሎች
  • ሥራዎች
  1. ጠቅላላ ጉባኤ

    ጠቅላላ ጉባኤው የኢመብም ከፍተኛ አስተዳዳሪ አካል ሲሆን ሁሉንም የተመዘገቡ አባላት ያቀፈ ነው።

    የጠቅላላ ጉባኤ አመራሮች

    • ትዕግስት ይልማ

      ትዕግስት ይልማ

      የምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሳቢ

    • ነዚፍ ጀማል

      ነዚፍ ጀማል

      የምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ም/ል ሰብሳቢ

    • ምህረት ካሳ

      ምህረት ካሳ

      የምክር ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ጸሐፊ

    ከፍተኛ አካል
  2. የምክር ቤት ቦርድ

    የምክር ቤት ቦርድ ስትራቴጂካዊ አመራርና ቁጥጥር ይሰጣል።

    የምክር ቤት ቦርድ አመራሮች

    • አማረ አረጋዊ

      አማረ አረጋዊ

      የምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

    • ታምራት ሀይሉ

      ታምራት ሀይሉ

      የምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ ም/ል ሰብሳቢ

    • ነብዩ ጥዑመልሳን

      ነብዩ ጥዑመልሳን

      የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

    • ሞላልኝ መለሰ

      ሞላልኝ መለሰ

      የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

    • መሠረት አታላይ

      የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

    ስትራቴጂካዊ አመራር
  3. ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ

    በጠቅላላ ጉባኤዎች መካከል ውሳኔዎችን ይተገብራል።

    ተግባራዊ ማድረግ
  4. ጽሕፈት ቤት

    ጽሕፈት ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎችን ይመራል።

    ዕለታዊ
§ V

ኮሚቴዎች እና ፓነሎች

የሚዲያ ደረጃዎችን እና የሙያ እድገትን የሚያንቀሳቅሱ ልዩ ኮሚቴዎች

ቋሚ ኮሚቴ · I

የስነ-ምግባር እና የሙያ ደረጃዎች ኮሚቴ

ለሚዲያ ሙያተኞች የሥነ-ምግባር መመሪያዎችን ያዘጋጃል።

ቋሚ ኮሚቴ · II

የቅሬታ አፈታት እና የሚዲያ ቅሬታ ሰሚ ፓናል

በሚዲያ ድርጅቶች ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን ይያዛል።

ቋሚ ኮሚቴ · III

የስልጠና እና አቅም ግንባታ ኮሚቴ

የሙያ ልማት ፕሮግራሞችን ይነድፋል ይተገብራል።

ቋሚ ኮሚቴ · IV

የጥናት እና ፖሊሲ አማካሪ ኮሚቴ

ምርምር ያደርጋል ለፖሊሲ ምክር ይሰጣል።

§ VI

ስራ አስፈጻሚ መሪዎች

አመራር

የምክር ቤት አመራር

  • i. ኦፊሰር

    ሊቀመንበር

    አጠቃላይ አመራር ይሰጣል እና ምክር ቤቱን ይወክላል

  • ii. ኦፊሰር

    ምክትል ሊቀመንበር (ዎች)

    ስትራቴጂካዊ እና የስራ ክንውን ክትትልን ይደግፋል

  • iii. ኦፊሰር

    የፕሮግራም እና ዋና ስራ አስኪያጅ

    አስተዳደርን፣ መዝገቦችን እና ቅንጅትን ይቆጣጠራል

አስተዳደር

የጽሕፈት ቤት አመራር

  • i. ኦፊሰር

    ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር

    የኢመብም ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች አፈፃፀምን ይመራል

  • ii. ኦፊሰር

    የፕሮግራም እና ስነ-ምግባር ኦፊሰሮች

    ፕሮግራሞችን ያስተዳድራል እና የስነ-ምግባር ደረጃዎችን ያስከብራል

  • iii. ኦፊሰር

    የህግ እና ቅሬታዎች ኦፊሰሮች

    የህግ ጉዳዮችን እና የቅሬታ አፈታትን ያስተናግዳል

  • iv. ቡድን

    የአስተዳደር እና ፋይናንስ ቡድን

    የአስተዳደር እና የፋይናንስ ስራዎችን ያስተዳድራል

ግብዣ

የምክር ቤታችን አባል መሆን ይፈልጋሉ?

የኢመብም አባል ይሁኑ — የፕሬስ ነፃነትና የሥነ-ምግባር ጋዜጠኝነት እንቅስቃሴ አካል።