እንስት ጋዜጠኞች በዲጅታል ሚዲያው ዘርፍ መጠናከር አለበት ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ገለፀ።
እንስት ጋዜጠኞች በዲጅታል ሚዲያው ዘርፍ መጠናከር አለበት ሲል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ገለፀ።በኢትዮጵያ መገናኛ ምክር ቤት የሰራ አስፈፀሚ ኮሚቴ አባል አቶ ሞላላኝ መለስ የሚዲያ ሚና እና የስነ ምግባር ህግን በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷዋል ።
በስልጠናው ላይ እንዳነሱት ጋዜጠኞች የስነ ምግባር ህግን ተከተለው መስራት አለባቸው ያሉ ሲሆን ለዚህም እንደ ሀገር የስነ ምግባር ደንብ እንዳለም አብራርተዋል ።
ፍትህታዊነት እና ሚዛናዊነት የጋዜጠኞችን ልዩ መገለጫ መሆን ይኖርበታል ያሉት አቶ ሞላልኝ ሁሉንም ስራዎች በተገቢ እውቀት ላይ ተንተርሶ በነጻነት መሰራት ይጠይቃል ብለዋል።
ተቋማትም ጋዜጠኞች ለሞያው ታማኝ እንዲሆኑ የራሳቸውን ሀላፊነት እንዲውጡም ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ከፈረንሳይ ተቋም ጋር በመተባበር ለእንስት ጋዜጠኞች በተዘጋጀው በዚህ ስልጠና ላይ የዲጅታል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ መፍጠር እንዳስቻላቸው እንዲሁም የፖድካስት ሚዲያ አጠቃቀም እና ስነ ምግባር በተመለከተ ግንዛቤ እንደፈጠራላቸው ስልጣኞቹ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብዙሀን መገናኛ ምክር ቤት ተወካይ አቶ ተድላ ሆራ በስተላለፉት መልዕክት የዲጅታል ሚዲያን በአግባቡ እና ስነ – ምግባርን በጠበቀ መልኩ መጠቀም ከተቻለ የራስን ገፅታ ከመገንባት በሻገር ወደ ገቢ ማስገኛ መቀየር እንደሚቻል ተናግረዋል ። አያይዘውም መሰል ስልጠናዎች ትልቅ አቅምን ይፈጥራሉ ብለዉ እንደሚያምኑ አስረድተዋል ።
የዲጅታል ሚዲያ እና ፖድካስት አሰልጣኝ አቶ አቤል በበኩላቸው የመጪው ዘመን አዳዲስ ለውጥ ይዞ እየመጣ ስለሆነ ህዝብን ለማስተማር እንደ ሀገር የዲጅታል ሚዲያ ላይ ተከታታይ የሆነ ስራን መስራት ተገቢ ነው ብለዋል ።
በድሬዳዋ በተዘጋጀው የሁለት ቀን ስልጠና ላይ ተሳታፊ የነበሩት የድሬዳዋ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ማህበር አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አንስታው ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ባሉ የክህሎት ስልጠናዎች ላይ የትኩረት መስክ በተመለከተ ውይይትም አድርጓል ። በመጨረሻ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ለተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ተበርክቶል፡፡